ያልተነገረው የአጣዬ እልቂትና ዋና አላማ-ወረራው የማንቂያ ደወል አሊያም የመጥፊያችን ማወጃ ክስተት የመሆኗ ታሪክ

 ያልተነገረው የአጣዬ እልቂትና ዋና አላማ-ወረራው የማንቂያ ደወል አሊያም የመጥፊያችን ማወጃ ክስተት የመሆኗ ታሪክ

***ወንድወሰን ተክሉ***
  •   በአጣዬ የተፈጸመው ምንድነው?? የከተማይቱና የህዝቡስ ሁኔታ ምን ይመስላል?
 በስፍራው ጉብኝት አድርገው ከተመለሱት የአይን ምስክሮች አንደበት
 
«የአጣዬ ከተማ በዛሬይቷ ኢትዮጲያ አንድ ከተማ ሙሉ በሙሉ ወድሞ ሰው አልባ የመንፈስ ከተማ መሆን የተቻለበት ስፍራ መሆናን የምታሳይ ከተማ ናት» የአባይ ሚዲያ ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ
 
«በአጣዬ ሰው ብቻ አይደለም የተገደለው ንብረት ብቻም አይደለም የወደመው፡ እንዳለ የከተማዋ ህይወት ነው የጠፋው፡፡የእርሰበርስ ተከባብሮ መኖር ኢትዮጲያዊነት እሴት የምንለው ሀብታችን ነው ሙሉ በሙሉ የወደመው»የአባይ ሚዲያው ጋዜጠኛ ቴውድሮስ
«ለተከታታይ ቀናት ጥይት እንደ በረዶ ሲዘንብብን የመንግስት ያለህ ድረሱልን ስንል የደረሰልን አንድም መንግስታዊ ኃይል የለም፡፡
 
 የመጣው መከላከያ እኛን ከመርዳት ይልቅ እየተሰው እኛን ለመከላከል ላይ ያሉ የአማራ ልዩ ኃይልን ከጀርባ ሆኖ በመምታት የያዙትን ገዢ የመከላከያ ስፍራን እንዲለቁ በማድረግ የኦሮሞ ታጣቂዎቹ ወደ ከተማችን ገብተው እንዲፈጁን አድርገዋል፡፡ እኛን የፈጀን እና ያስፈጀን መንግስት ነው፡» በአጣዬ ጭፍጨፋ ሰለባ ተራፊዎች ውስጥ አንዷ እናት በስፍራው ለተገኘው የጋዜጠኞች ቡድን የተናገሩት
«የጭፍጨፋው ወረራ ዋና አላማ በጃዋር የተሰራውን እስከወሎ የሚደርስ የኦሮሚያን ካርታ የመስራት ዘመቻ ይመስለኛል፡፡ አጣዬ ደግሞ ያለችው ወሳኝ እስራቴጂክ ቦታ ስለሆነ ስፍራውን ሙሉ በሙሉ አጽድቶ ሌሎችን አምጥቶ ለማስፈር ያለመ ይመስላል » የአጣዬ ከተማ ምክትል አስተዳደር ለጋዜጠኞች የተናገሩት
 
«እኛ ደጋግመን ባህርዳር ላለው የአማራ ክልል እና ለፌዴራሉ ጸጥታና ደህንነት ቢሮ (በአቶ ተመስገን ጥሩነህ ለሚመራው) የወራሪዎቹን ዝግጅት ነግረናል፡፡ ከከሚሴ ተነስተው ገና ማጀቴ ሲደርሱ ድረሱልን ኃይል የለንም ብለን እየደወልን ወትውተናል፡ ወራሪዎቹ አጣዬ ከደረሱ በኃላም አሳውቀናል -የእኛ ጩህት ሲበዛባቸው አዲስ አበባ ያሉትም ሆነ ባህርዳር ላይ ያሉት ስልካቸውን አጥፍተው ጭጭ ያሉን ሆነዋል» የአካባቢው አመራር አባል
 
«ቀናት በፈጀው ውጊያ በእኛ በኩል ጥይት ሲያልቅ በእነሱ በኩል ጥይት ብቻ ሳይሆን አዲስ ተተኪ ተዋጊ ኃይል በገፍ እየቀረበላቸው በአዳዲስ ጉልበት ከመድፍ በስተቀር በቡድን ከባድ መሳሪያ ድጋፍ በከበባ መልክ ሌት ተቀን የጥይት ናዳ አዝንበውብን ነው የጨፈጨፉን » የአካባቢው ሚሊሻ አባል ለጋዜጠኞች እንደተናገረው
  •  የአጣዬ ጥቃት ለምንና እንዴት ተፈጸመ ???
 
ከከሚሴ እስከ ሸዋሮቢት 80ኪ ሜ ራዲየስ በሚሸፍን ስፋት ውስጥ በሶስት ወረዳዎችና በአምስት ከተሞች ላይ በተከፈተው ስድስት ቀን የፈጀ የወረራ ጦርነት አጣዬ ካራቆሬ ማጀቴ ሸዋሮቢት ጦቢት 44677 የሚባሉ ከተሞች ኢላማ የተደረጉ ሲሆን ከእነዚህ ከተሞች ውስጥ ከ90-100ሺህ ነዋሪዎች ያሉባት የአጣዬ ከተማ ግን ሙሉ በሙሉ 100% የወደመች ሲሆን ካራቆሬና ጡቢት$--88 ግን አብዛኛው የከተማው ክፍል የወደመባቸው ሆነዋል፡፡
 
ከስድስት ቀናት በላይ በፈጀው የጭፍጨፋ ውጊያ ያለቀውን የሰው ቁጥር ሙሉ በሙሉ እስከዛሬ ድረስ ቆጥሮ ማወቅ እንዳልተቻለ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ተራራው ላይ በየጢሻው ሽር እሬሳ ሞልቷል፡፡ እስካሁን ያልተቀበረና በጅብም ያልተበላ አስከሬን አለ ያሉት ነዋሪዎቹ በዚህ በአገባደድነው ሳምንት አጋማሽ ላይ (ሚያዚያ 25/6 -2021)ሲሆን ጭፍጨፋው የተፈጸመው ግን በወሩ መግቢያ ላይ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እንደ ዶ/ር ሲሳይ የሰሜን ሸዋ የሰላም ተራድኦ በጎ አድራጊ ማህበር ሊ/ር አገላለጽ ደግሞ እስካሁን ከ270በላይ አስከሬኖችን መቅበር የተቻለ መሆኑንና ከ260ሺህ በላይ ደግሞ ከአምስቱ ከተሞች መፈናቀሉን ይገልጽና በአጣዬ ብቻ ከ7600በላይ ቤቶች መቃጠላቸውን መመዝገብ ችለናል ይላል፡፡
 
ከ7600በላይ ቤቶች ተቃጥለው የወደሙባት የአጣዬ ከተማ ዛሬ ለተምሳሌት እንኳን የሚሆን አንድም ሰው የማይኖርባት ፍጹም ባዶ የመናፍስት ከተማ $#-**/ በመሆን በዛሬይቷ ኢትዮጲያ አቢይ አህመድ መራሹ የኦህዴድ ብልጽግና መንግስት ዘመን የሰው ልጅን ሰይጣናዊ አረመኔነትን አሻራ የምታሳይ የሰዶም ከተማ ሆናለች፡፡

 
በከተማይቱ ውስጥ ዳር ዳር ያሉና የድህ ቤቶች የሆኑ በጣት የሚቆጠሩ ደሳሳ ጎጆዎች ቁሳቁሳቸው ተዘርፎ ባዶ ወና ሆነው ለመታየት ከበቁት በቀር በከተማዋ ውስጥ የነበሩት እንደነ ባንክ የአስተዳደር ተቋማት የህክምና ማእከል ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የግል ንግድ ቤቶችና መኖሪያ ቤቶች በሙሉ ተዘርፈው ሙሉ በሙሉ ወድመው ከተማይቱ በእርሰበርስ ጦርነት እንደወደመችው የ1990ዎቹ ሞቃዲሾና የዘመናችን ሶሪያ አሌፖ ከተሞች ሆና የሙታን መንደር መስላለች፡፡ የወደመች ባዶ -ፍጹም የሆነ ባዶ፡፡ አንድም ሰው እንኳን እማይኖርበት ፍጹማዊ ባዶ ከተማን ከአዲስ አበባ 270ኪ ሜ ርቀት ላይ የአቢይ መራሹ የብልጽግና መንግስት ለቅርስነት መፍጠር ችሏል፡፡
 
ይህ የተፈጸመበትን መንገድ ማወቁ ደግሞ ሌላኛው የወረራውን አረመኔነትና ጨካኝነትን የሚገልጽ ነው፡፡ ባለስናይፐሮቹና ባለመትረየሶቹ ወራሪዎች አካባቢውን ሲወርሩ ማለትም ከላይ በተጠቀሰው ሶስት ወረዳዎች ውስጥ ባሉት አምስቱ ከተሞች ማለት ነው እነሱ ከፊት እየተታኮሱ ወደፊት ሲገፉ ከኃላቸው ምንም ያልታጠቀ ባዶ እጅ መንጋ ቤኒዚን እና ማጓጓዣ ይዞ ይከተላቸዋል፡፡ እንደ የአጣዬ ከተማ ሰለባዎች ምስክርነት እነዚህ ምንም ያልታጠቁ መንጋዎች ከተጎራባቾቹ የአማራ ክክል የኦሮሚያ ዞን የመጡ ኦሮሞዎች ናቸው ሲሉ ይገልጿቸዋል፡፡ ከዚያም ታጣቂዎቹ ወደየከተማው በመግባት ያገኙትን ትንሽ ሆነ ትልቅ የሆነን ወንድ ሁሉ በወንድነቱ እየለዩ ሲገድሉ ሲጨፈጭፉ እነዚህ ምንም ያልታጠቁት ደግሞ ቤቶችን እየዘረፉ በእሳት የማጋየቱን ስራ ይፈጽማሉ፡፡ በእነደዚህ የተቀናጀ ዘመቻም ከተሞችን አውድመው የዘረፉትን ጭነው እየተንፈላሰሱ ወደ መጡበት ተጎራባች የኦሮሞ ዞን ይሄዳሉ፡፡
 
የወራሪዎቹ ኢላማ ከትንሽ እስከትልቅ ወንድ ብቻ የሆነበትን እና በተመሳሳይ ሁኔታ በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፎና ብሎም አቃጥሎ ሰውን መግደልና በመንጋ ዘመቻ አጠቃላይ የከተሞቹንና መንደሮችን ሁለንተናዊ ቁስ ዘርፎ መሄድ ጥንት በ16ኛውና በ17ኛው ክፍለ ዘመን ከተፈጸመው የኦሮሞ መስፋፋት ዘመቻ ጋር ፍጹማዊ አንድነትና ተመሳሳይነት ያለው ስልት ሆኖ ይታያል፡፡
 
ኦሮሞ ይህንን አይነቱን የመስፋፋትን ዘመቻ ሲያደርግ ወንድ ወንዱን ከህጻን እስከ አዛውንት በመግደል ሀብት ንብረቱን በመዝረፍ ሴቶችን ደግሞ እንዳለ በመውረስ በሚስትነትና በባሪያ አገልጋይነት የመጠቀምን ስልት በመጠቀም ሲሆን በዚህ በሰሜን ሸዋ ወረራ ያልተፈጸመ ነገር ቢኖር የተዋቸውን ሴቶችን ጭነው ያለመሄዳቸው ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እራሱን የቻለ ግብ ተይዞለት የተተው ሆኖ እናያዋለን፡፡ የወረራው የመጨረሻ ግብ ወንዶችን ጨፍጭፎ ከተማና መንደሮችን አውድሞ ንብረቶችንም ዘርፎ ሴቶቹን ትቶ ዘወር የማለቱ ተግባር ባወደሟቸው መንደሮችና ከተሞች ውስጥ ተመልሰው በመስፈር ባል አባትና ወንድም አልባ የሆኑትን ሴቶችን በሚስትነትና በሰራተኝነት በመያዝ ሀገሩን የሚለማመዱበት በማድረግ ነውና ዛሬ ከተሞችን ከሰው አጽድተው ሰው አልባ ማድረግ የቻሉ ሲሆን ቀጣዪ እርምጃቸው ደግሞ ይህንን ባዶ ያደረጉትን ከተማና መንደር ማንም ተመልሶ እንዳይሰፍርበት በማድረግ ባዶ እንደሆነ ትንሽ ጊዜ አቆይቶ እራሳቸው ሄደው መስፈር ነው፡፡ ይህንን ለመፈጸምስ ምን እየተሰራ ነው??
 
👉 ምድረ በዳ በሆነችው የአጣዬ ከተማ ወረሪውን መልሶ ለማስፈር እየተሰራ ያለ ወቅታዊና መንግስታዊ ስራ
 
« እኛ ከአጣዬ ለቀን ወደ አዲስ አበባ እየተጓዝን ሳለና ከዚያው አጣዬ አካባቢ ሳንለቅ የኮማንድ ፖስቱ ኃላፊ የተባሉ ጄኔራል በአጣዬና አካባቢዋ የነበረው ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ወደ መረጋጋት በመመለሱ ነዋሪዎች ወደየቤታቸው እየተመለሱ ነው የሚል መግለጫ ሲተላለፍ ሰማንና እጅግ ደንግጠን እርሰብርሳችን ተያየን» ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ በማለት በፍርስራሽነቷና በባዶነቷ እኛንም አስፈራችን ባለቻት አጣዬ ከተማ እዚያው ባሉበት የጄኔራሉን መግለጫ በድንጋጤ እንድትሰማ ያደረጋት የኦህዴድ ብልጽግናን አላማ ባለማወቅና እዚያው ስፍራው ላይ ሆና እውነቱን በማየቷ ነው እንጂ የመግለጫው አላማ ነዋሪዎቹ ተመለሱ ወይም እየተመለሱ ነው በማለት የራሳቸውን ሰፋሪ እያመጡ በማስፈር ከተሟይቱን የመውረስን አላማ ለመተግበር ሲሉ ያስተጋቡት ዜና ነው፡፡
 
የሙታን ፍርስራሽ ከተማ የሆነችውን አጣዬን እያስተዳደረ ያለው ኮማንድ ፖስቱ ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል ነዋሪውን በሙሉ ወደ ጫካ ማባረርና (በእርግጥ በወራሪው የተባረረውን) እዚያው ጫካው እንዲቀር መሳሪያ ይዞ ወደ ከተማው 20ኪ ሜ መቅረብ አይቻልም የሚለውን ህግ ማውጣት ነው፡፡ ይግ ህግ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱት የአማራ ልዪ ኃይል አባላትም ላይ ተፈጻሚ በመሆኑ አንድም የአማራ ልዩ ኃይል አባል መሳሪያ ታጥቆ ወደ ከተማው እንዳይገባ ታግዷል፡፡ ነፍሱን ለማትረፍ ተፈናቅሎና ሸሽቶም ያለው የከተማዋ ባለቤትና ነዋሪም እራሱን መጠበቂያ አንድ መሳሪያ ይዞ ወደከተማው እንዳይገባ ኮማንድ ፖስቱ ህግ አውጥቷል፡፡
 
ከአቢይ መራሹ መንግስት ወደ ስልጣን መምጣት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ ከስድስት ጊዜ በላይ ከፍተኛ ወረራና አሁን መጨረሻ ላይ ደግሞ አጠቃላይ ውድመት የተፈጸመበት የአጣዬ ከተማ ነዋሪ በደረሰበት ተደጋጋሚ ጭፍጨፋና እሱ እራሱ በአይኑ ባየውና ባረጋገጠው መረጃና ማስረጃ መሰረት ወረራው መንግስታዊ ወረራና ጭፍጨፋ ነው ብሎ በማመኑ መንግስትን ቅንጣት ታህል የሚያምን አልሆነም፡፡ መንግስት ተብዬውም እንዳይታመን ያደረገውን የክህደትን ስራ ደጋግሞ እየፈጸመ ያለ በመሆኑ በህዝቡ ባይታመን አይደንቅም፡፡ ምስጢሩ ግን ይህ በመንግስት ላይ እምነት የሌለውን ህዝብ መሳሪያህን ጥለህ ወደፈራረሰችው የአጣዬ ከተማ ግባ ማለት ዳግመኛ ወደዚህ ዝር እንዳትል ብሎ የማገድ ያህል ማለት ነው፡፡ እናም ህዝቡን በዚህ መንገድ ያገደውና እያራቀ ያለው ኮማንድ ፖስት በተመሳሳይ ሁኔታ አካባቢው ተረጋግቶ ነዋሪው ወደ ቀዬው እየተመለሰ ነው ብሎ መግለጫ ማውጣት ትርጉሙ አሁን የምንረዳ ይመስለኛል፡፡
 
«የእርሰበርስ ግጭት የሚባል ነገር አይደለም፡፡ እኛን የጨፈጨፈን ከእኛጋር ያለው ኦሮሞም አይደለም፡፡ ይህ ለየት ያለ ኦሮሚኛ የሚናገር እጅግ የሰለጠነ ህንጻ ሳይቀር ማውደም የቻለ ከባድ መሳሪያ የታጠቀ በመንግስት በሚደገፍ ታጣቂ ነው፡፡ የተጨፈጨፍነውም በአማራነታችን እንጂ ከጎናችን ኦሮሞ ሆነው ያልተነኩትን አይተናል፡፡ በመተከል ቢገደል አማራ ነው፤ በወለጋ እሚገደለው አማራ ነው፡፡ በአጣዬም እሚገደለው አማራ ነው፡፡ አጣዬ በሶሪያ ተፈጸመ ተብሎ የምንሰማው እልቂት በእኛው ላይ መጥቶ የተፈጸመባት ከተማ ናት፡፡ እኔ የሰባት ልጆች እናት ሴት ብሆንም ታጥቄ እራሴን ለመከላከል ግዴታዬ ነው፡፡ የሚገድለን እንጂ የሚሰማን መንግስት እንደሌለ አውቃለሁ፡፡ የምትሰሙን አማራ ካላችሁ እራሳችንን እንድንከላከል በማስታጠቅና በማደራጀት እንድትረዱን እጠይቃለሁ» አንዲት የጭፍጨፋው ሰለባ እናት ፡፡
 
«በአጣዬ ላለው ህዝብ የሚበላ ስንዴ ዘይት መርዳት ሳይሆን እራሱን የሚከላከልበትን መንገድ መርዳት ማደራጀትና ማስታጠቅ ያስፈልጋል» ስሙን መጥቀስ እማልፈልገው የአካባቢ ባለስልጣን በሶስት ወረዳዎችና በአምስት ከተሞች ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ወረራዊ ጭፍጨፋ ከተፈጸመ ከሃያአምስት ቀናት በላይ ቢሆነውም እስከዛሬዋ ድረስ አካባቢውን ሄዶ መጎብኘት የቻለ የአካባቢው ተወላጆች የኤፌሶን በጎ አድራጎት ማህበራት ሸዋ የሰላም በጎ አድራጎት ማህበርና መሰል በሆኑ በጎ አድራጊዎች አስተባባሪነት የግል ጋዜጠኛ ቡድን በዚህ ሳምንት አጋማሽ ወደ አካባቢው ከመጓዙ በቀር አንድም የሆነ የፌዴራሉም ሆነ የክልሉ (የአማራ ክልል ) ባለስልጣን ሄዶ አልጎበኘውም፡፡ለተፈናቀለው ከ260ሺህ በላይ ተፈናቃይም እስካሁን የተላከ ቅንጣት ታህል መንግስታዊ ድጋፍ የለም፡፡ በሸዋሮቢት ለሰፈረው ተፈናቃይ ህዝቡ ያለውን እያካፈለ ተፈናቃዮችን እየመገበ ያለ ሱሆን በአጣዬ ጫካ ውስጥና መጠለያ ጣቢያ ያለውን ደግሞ እንደ የኤፌሶን በጎ አድራጎት ማህበርና ሸዋለሰላም በጎ አድራጎት ማህበር በግል ተነሳሽነት ከሚያደርጉት ድጋፍ በስተቀር ማንም የደረሰላቸው የለም፡፡
 
👉 መደምደሚያ 
 
አጣዬ የጥላቻ አረመኔነትና በአማራ ላይ የተደገሰውን ትልቁን ሰይጣናዊ ድግስ ግፍ ቀማሽና በአጠቃላይ በኢትዮጲያ ላይ የሚፈጸመውን አሰቃቂ ወንጀሎች ቁልጭ አድርጋ የምታሳይ ምስክር ናት፡፡ አንድም መንግስታዊ የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን አልሰጧትም፡፡ በስልጣን ፍቅር የሰከረው ዘረኛውና ፋሺስቱ የብልጽግና መንግስት በተለይ በተለይ ኦህዴድና ብአዴን የተስማሙትን የተስፋፊዋን ኦሮሚያን ግንባታን ምስጢርን ፍንትው አድርጋ የምትመሰክርም ነች አጣዬ፡፡ እጅግ የበተውን የገለማውን የሰውን ልጅን አረመኔነትን የተመስገን ጡሩነህንና የአማራው ተወካይ ነኝ የሚለውብ ብአዴንን ፍጹማዊ ጸረ አማራነትና የህዝቡንም ህልውናን ለከርሳቸውና ስልጣናቸው መሸጣቸውን ቁልጭ አድርጋ የምትመሰክር ናት አጣዬ፡፡
 
አጣዬ በማንነቱ ላይ ጦርነት ታውጆበት ህልውናውን ለማዳን ማድረግ የሚገባውን የአጸፋን እርምጃ ባለመውሰድ ዝም ብሎ እያየና እየተኛ ያለውን መላውን የአማራን ህዝብ ዳተኝነትና ተንቀርፋፊነትንም ያለአንዳች ይሉኝታ እያጋለጠች የምታሳይም ከተማ ነች፡፡
 
👉 አዎን አጣዬ በሚቀጥሉት ወራቶች ውስጥ ኢትዮጲያ እንደ ሀገር አማራውም እንደ ብሄር በቀጣይ ወራቶች የሚገጥማቸውን በቀዳሚነት የምታሳይም ማንቂያ አሊያም እልቂቱን ማወጂያም የሆነች ከተማ ነች፡፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ በተለይ በተለይ እያንዳንዱ አማራዊ ዛሬ በሚጋዝበት የህይወት የፖለቲካና የአጠቃላይ አመለካከት ጎዳና ላይ መጓዙን ከመቀየርና አዲስ ይህንን ክስተት የሚመጥን አካሄድ ለመጓዝ ካልመረጠ አጣዬ ማለት የነገው አማራና ኢትዮጲያ ማለት መሆኑን የምትገልጽ ከተማም ነች፡፡
 
👉 የአቢይ መራሹን ኦህዴድንን ገደብ የለሽ ሰይጣናዊ ጸረ አማራን አቋምና ሰይጣናዊን የተስፋፊነትን ወረራን አላማና ቁርጠኝነትን ቁልጭ አድርጋ በምታሳየን አጣዬ ዛሬ ወሳኝ እርምጃ ካልወሰድን ጥፋቱ የእኛ የመላ ኢትዮጲያዊያን እና በተለይም እንደ ህዝብ የእኛ አማራዊያን እንደሚሆኑ ሁሉም በአጽንኦት ሊያውቀው የሚገባ ሀቅ ነው፡፡
 
👉 አጣዬ የማንቂያ ደውል ነች አሊያም የእልቂታችንን ማወጂያም ፍርድ ነች!!!

 
 
 

 

0/Post a Comment/Comments